ይህ ቪዲዮ በIELTS የንግግር ፈተና ላይ ትኩረት የሚሰጥባቸውን የቃላት ክምችትንና የቃላት እውቀትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ያብራራል። እንዲሁም ተጣምረው ትርጉም ስለሚሰጡ ቃላት፣ እንደ አገባባቸው ትርጉም ስለሚሰጡ ቃላት፣ አንድን ሃሳብ በተለየ አነጋገር ስለ መግለፅና ብዙም ያልተለመዱ ቃላት አጠቃቀምን ጭምር ያብራራል።